በዓልን በመተጋገዝና በመረዳዳት በጋራ ማሳለፍ ማህበራዊ አብሮነትን ይበልጥ ከፍ እንደሚያደርግ ተገለጸ

You are currently viewing በዓልን በመተጋገዝና በመረዳዳት በጋራ ማሳለፍ ማህበራዊ አብሮነትን ይበልጥ ከፍ እንደሚያደርግ ተገለጸ

AMN-ግንቦት 20/2018 ዓ.ም

1447ኛውን የኢድ አል አድሃ አረፋ በአልን በማስመልከትም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር በጀሞ 1 ሸራ መስጂድ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ተካሄዷል፡፡

ወ/ሮ ለይላ ሰማ በአዲስ አበባ ብሄረጽጌ አካባቢ ነዋሪ ናት፡፡ የስኳር ታማሚ መሆኗን የምትናገረው ወ/ሮ ለይላ ምንም እንኳ የራሷ ገቢ እና ለበዓል ሸመታ የምታከናውንበት ጥሪት ባይኖራትም የሚሰጡ እጆችን በማዘጋጀት ፈጣሪ አስቦኛል ስትል ገልጻለች፡፡

ሌሎች የማዕድ ተጋሪዎችም ለሰጡ እጆች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የኢስላሚክ ሪሊፍ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር አቶ አህመድ ሞሃመድ በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ ለአረፋ በአል ከ12 ሺህ በላይ ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች የማዕድ ማጋራት መከናወኑን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ልማት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ጅደዲን ሰይድ በበኩላቸው በዓሉን ሁሉም ሰው እኩል ተደስቶ እንዲሳልፍ በሚል ሃሳብ ዝቅተኛ አቅም ያላቸውን ታሳቢ ባደረገ መልኩ የማዕድ ማጋራቱ መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡

በዓልን በመተጋገዝና በመረዳዳት በጋራ ማሳለፍ ማህበራዊ አብሮነትን ይበልጥ ከፍ እንደሚያደርግ ነው የመርሃ ግብሩ አዘጋጆች የገለጹት፡፡

1447ኛውን የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓልን ምክንያት በማድረግ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብሩን ያዘጋጁት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ልማት ኤጀንሲ ከኢስላሚክ ሪሊፍ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር መሆኑም ተገልጿል፡፡

በምትኩ ተሾመ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review