ኢትዮጵያ በ2027 የሚካሄደውን ዓለም አቀፍ የፀረ-ዶፒንግ ትምህርት ጉባኤ እንድታዘጋጅ ተመረጠች

AMN- ሰኔ 6/2018 ዓ.ም

የዓለም አቀፉ የፀረ-ዶፒንግ ትምህርትና ስልጠና ጉባኤ (Global Education Conference) በዓለም አቀፉ የፀረ-ዶፒንግ ኤጀንሲ (WADA) አዘጋጅነት በየጊዜው በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ኢትዮጵያም እ.ኤ.አ በ2027 የሚዘጋጀውን ጉባኤ እንድታስተናግድ መመረጧን የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

default

ይህ በፀረ-አበረታች ቅመሞች እንቅስቃሴ ዙሪያ ከፍተኛ አንድምታ ያለው ኩነት ፣ ቀደም ሲል እ.ኤ.አ በ2018 በቻይና ቤጂንግ ፣ በ2022 በአውስትራሊያ ሲድኒ እንዲሁም በ2024 በፈረንሳይ ተካሂዷል፡፡ የዓለም አቀፉ የፀረ-ዶፒንግ የትምህርት ጉባኤ በአፍሪካ ደረጃ ሲካሄድ ግን የመጀመሪያው ይሆናል፡፡

ጉባዔው ለሀገር ገፅታ ግንባታ እና የስፖርት ቱሪዝም እድገት ከሚያበረክተው አስተዋፅኦ በተጨማሪ በአህጉር አቀፍ ደረጃ የፀረ-አበረታች ቅመሞች እንቅስቃሴውን የበለጠ በማጎልበትና ንፁህ ስፖርትን በማስፋፋት ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረክታል ተብሎ ታምኖበታል።

በሌላ በኩል ኢትዮጵያ አበረታች ቅመሞችን የሚመለከቱ ጉዳዮችን በመደበኛ የትምህርት ስርዓት ውስጥ አካትቶ መተግበርን ፣ በቂ የህግ ማዕቀፎችን በማውጣት ተግባራዊ ማድረግን ፣ ጠንካራ የምርመራና ቁጥጥር ስርዓት መዘርጋትና ተግባራዊ ማድረግን ጨምሮ የተመዘገቡ በርካታ ውጤቶችን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በአግባቡ ለማስገንዘብ ዕድል እንደሚፈጥር ባህል እና ስፖርት ሚኒስትር አስታውቋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review