የምንግዜም ምርጥ ክርክሩ አበቃለት ወይስ CR7 በአለም ዋንጫው ያንሰራራ ይሆን?

AMN- ሰኔ 10/2018 ዓ.ም

በትናንትናው ምሽት ሊዮኔል ሜሲ በዓለም ዋንጫ ታሪኩ የመጀመሪያውን ሀትሪክ ሰርቶ፣ የ16 ግቦች የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ክብረወሰንን ሲጋራ ሁላችንም በአድናቆት አይተናል። ታዲያ ይህ የሜሲ ድንቅ ስኬት ዛሬ ምሽት ሜዳ ለሚገባው የዘመናት ተቀናቃኙ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ትልቅ ማገዶ እንደሚሆነውና የቀድሞውን የላሊጋ ወርቃማ ዘመን የፊት ለፊት ፉክክር ከ4 ዓመታት በኋላ መልሶ እንደሚቀሰቅሰው በከፍተኛ ጉጉት ይጠብቅ ነበር።

ሁለቱ ከዋክብት በጋራ 13 የባሎን ዶር (ሜሲ 8፣ ሮናልዶ 5) በመውሰድ እግር ኳስን በበላይነት የገዙበት ዘመን ሁሌም ቢወሳም፣ የዛሬው ምሽት ግን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ ፈጽሞ የተጠበቀው አልሆነም።

የሮናልዶ አስደንጋጭ የሙሉ ሰዓት አኃዞች፦

* ⚽ 25 ንክኪዎች ብቻ (በዓለም ዋንጫ ታሪኩ በቋሚነት ጀምሮ 2ኛው ዝቅተኛው!

* 3 ሙከራዎች (0 ኢላማውን የጠበቀ)

* ⚽1 ፍልሚያ (Duel) ማሸነፍ

የሜሲ ትናንት ማብራት የሮናልዶን ስፖርታዊ ቁጭት ያነሳሳል የተባለው ግምት ሳይሳካ ቀርቶ፣ የኮንጎ ድንቅ መከላከል ምሽቱን ለሲ አር ሰቨን (CR7) እና ለፖርቱጋል እጅግ ቀዝቃዛ አድርጎታል።

ለመሆኑ የጎት (GOAT) ክርክሩ በይፋ አብቅቶለታል ማለት ይቻላል? ወይስ ሮናልዶ በቀጣይ ጨዋታዎች በአስደናቂ ሁኔታ ያንሰራራ ይሆን?

የእርስዎን አስተያየት ያጋሩን!!

በኪዳኔ በየነ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review