በዩጂን ዳይመንድ ሊግና በፒችትሪ የጎዳና ሩጫ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ

You are currently viewing በዩጂን ዳይመንድ ሊግና በፒችትሪ የጎዳና ሩጫ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ

AMN- ሰኔ 28/2018 ዓ.ም

በ2026 የፕሪፎንቴይን ክላሲክ- ዩጂን ዳይመንድ ሊግ እና በአሜሪካ የፒችትሪ የጎዳና ሩጫ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸንፈዋል። በአሜሪካዋ ዩጂን በተካሄደው የዳይመንድ ሊግ የሁለት ማይል ርቀት ውድድር አትሌት አለሺኝ ባወቀ በአሸናፊነት አጠናቅቃለች፡፡

አትሌቷ ውድድሩን በበላይነት ያጠናቀቀችው የወቅቱ ፈጣን የሆነ ሰዓት 9 ደቂቃ ከ20 ሴኮንድ ከ02 ማይክሮ ሴኮንድ በማስመዝገብ ነው፡፡ ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ሒሩት መሸሻ 9 ደቂቃ ከ20 ሴኮንድ ከ20 ማይክሮ ሴኮንድ በሆነ ሰዓት 2ኛ ደረጃ ይዛ ውድድሯን አጠናቃለች፡፡

በዚሁ ርቀት የተሳተፉት አትሌት ማርታ አለማየሁ 4ኛ፣ አትሌት የኔዋ ንብረት 7ኛ እንዲሁም አትሌት አሳየች አይቼው 8ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቀዋል።

በሴቶች የአንድ ማይል ውድድር ላይ የተሳተፉት አትሌት ሳሮን በርሀ በ4:22.50 11ኛ ደረጃን እንዲሁም አትሌት ወርቅነሽ መሰለ በ4:36.80 13ኛ ደረጃን ይዘው ፈፅመዋል።

በሌላ በኩል የአሜሪካ የነጻነት ቀን ክብረ በዓል አካል ሆኖ በተካሄደው በ57ኛው የፒችትሪ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር አትሌት ፅጌ ገብረሰላማ በ31:02 በሆነ ሰዓት በመግባት ውድድሯን በአሸናፊነት እንዳጠናቀቀች የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ሌላኛዋ አትሌት መልክናት ውዱ በሰከንድ ልዩነት ማለትም በ31:03 ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review