ኤ ኤም ኤን የትውልዱ ጥያቄዎች እንዲመለሱ በትጋት እየሰራ ነው

You are currently viewing ኤ ኤም ኤን የትውልዱ ጥያቄዎች እንዲመለሱ በትጋት እየሰራ ነው

AMN- ሰኔ 28/2018 ዓ.ም

የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የህዝብና የወጣቱ እውነተኛ ድምፅ በመሆን የትውልዱ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ በትጋት እየሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አሰግደው ኃይለጊዮርጊስ ገለጹ።

ኤ ኤም ኤን ከአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር “አሸናፊ ትውልድ” በሚል መሪ ሃሳብ ያዘጋጀው የ5 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር ተካሂዷል፡፡

በወቅቱ ኃላፊው እንደገለጹት፤ የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ራሱን በቴክኖሎጂ፣ በአሰራርና በአደረጃጀት አጠናክሮ በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱ ውጤታማ ተቋማት አንዱ ለመሆን በቅቷል።

አቶ አሰግደው አክለውም፤ ከተማዋን ውብ፣ ስማርትና ስሉጥ ለማድረግ እንዲህ አይነት ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ያላቸው ሚና እጅግ ከፍተኛና አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።

ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሁልጊዜም ከወጣቱ ጋር አብሮ የሚውል አካል ነው ያሉት ኃላፊው ከትውልዱ ጋር በመሆን የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ሁሉ በስኬት ለማጠናቀቅ ቢሯቸው ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።

በትዝታ መንግስቱ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review