ትውልደ ኢትዮጵያዊው የካናዳ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ዓሊ አህመድ የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኘ

You are currently viewing ትውልደ ኢትዮጵያዊው የካናዳ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ዓሊ አህመድ የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኘ

AMN – ሐምሌ 14/2018 ዓ.ም

በእንግሊዝ ለኖርዊች ሲቲ እግር ኳስ ክለብ እየተጫወተ የሚገኘውና በ2026 እ.ኤ.አ የፊፋ ዓለም ዋንጫ ለካናዳ ብሔራዊ ቡድን በአራት ጨዋታዎች ላይ የተሳተፈው ዓሊ አህመድ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ የቱሪስት መዳረሻዎችን እየጎበኘ ይገኛል፡፡

ከጎበኛቸው መዳረሻዎች መካከል የዓድዋ ድል መታሰቢያ አንዱ ሲሆን፤ ጀግኖች አባቶች እና እናቶች የከፈሉትን መስዋዕትነት የሚያሳዩ የታሪክ አሻራዎችን እና ቅርፃ ቅርፆችን ተዘዋውሮ ተመልክቷል፡፡

ተጫዋቹ የስፖርት ተሳትፎን ለማበረታታት እና በኢትዮጵያ የስፖርት ልማት ላይ አዎንታዊ አሻራ ለማሳረፍ የቀረበለትን ጥያቄ በደስታ ተቀብሎ ወደ ኢትዮጵያ እንደመጣ ተናግሯል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር፣ የቱሪዝም ሚኒስቴር እና የኢትዮጽያ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ዓሊ አህመድ በኢትዮጵያ የሚያደርገው ቆይታ የተሳካ እንዲሆን የጋራ ሥራዎች በማከናወን ላይ እንደሚገኙ ከዓድዋ ድል መታሰቢያ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review