በብዝሃነት የደመቀዉ የኅብር ቀን

You are currently viewing በብዝሃነት የደመቀዉ የኅብር ቀን

AMN – ጳጉሜን 4/2018 ዓ.ም

የአዲስ ዓመት መሸጋገሪያ ከሆኑት የጳጉሜን ቀናት መካከል አንዱ የሆነውና የኢትዮጵያውያንን ውብ ኅብረ-ብሔራዊ አንድነት፣ አብሮነትና የባህል ብዝሃነት የሚያጎላው የህብር ቀን ጳጉሜን 4 በሀገር አቀፍ ደረጃ ሲከበር ውሏል።

ከሰማንያ በላይ ቋንቋዎችና በርካታ ብሔር ብሔረሰቦች በጋራ ታሪክ የተሳሰሩባት ኢትዮጵያ፣ በልዩነቷ ውስጥ ያላት ውበት ለጠንካራ አንድነትና ለሉዓላዊነት የጸና ምሰሶ ሆኗታል።

የህብር ቀን መከበርም ብዝኃነትን በሚያጸና የጋራ ትርክቶች ለማጠናከር እንዲሁም የህዝብን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል።

ዕለቱ የኢትዮጵያ ሕዝቦች የጸና ማኅበራዊ መስተጋብር ማሳያ በሆኑት ድንቅ ባህላዊ አልባሳት፣ ማራኪ የሙዚቃ ቅንብሮች እና የኪነ-ጥበብ ስራዎች ቀርበውበታል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያዊነት መገለጫ በሆነው የማዕድ ማጋራት፣ አብሮነትን በሚያጸኑ ውይይቶችና በጎ አድራጎት ተግባራት ታጅቦ መዋሉ የዕለቱን ድምቀት ከፍ አድርጎታል።

በተለይም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አገር በቀል እሴቶችን በመጠቀም አብሮነትን፣ መረዳዳትንና ሰው ተኮር ተግባራትን ሲያከናውን የዋለ ሲሆን፤ ይህን ተግባር ማከናወን ከጀመረ ወዲህ የበርካቶችን ማህበራዊ ትስስር ማጠናከር ችሏል።

ከተማ አስተዳደሩ፤ ባህል እየሆነ የመጣውን ይህንን የመረዳዳትና የመደጋገፍ ድንቅ ተግባር ከባለሀብቶችና ማህበራት ጋር በመቀናጀት ነው እያከናወነ የሚገኘው፡፡

በበረከት ጌታቸው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review