የኢትዮጵያ ጥንካሬ በብዝሃነትና ሕብረ-ብሔራዊ አንድነት ላይ የፀና ነው

You are currently viewing የኢትዮጵያ ጥንካሬ በብዝሃነትና ሕብረ-ብሔራዊ አንድነት ላይ የፀና ነው

AMN – ጳጉሜን 4/2018

የኢትዮጵያ ጥንካሬ በብዝሃነትና ሕብረ-ብሔራዊ አንድነት ላይ የፀና መሆኑን የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ ገለጹ፡፡

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ጳጉሜን 4 “የሕብር ቀን”ን በማስመልከት ልዩ የኪነ-ጥበብ ምሽት አከናውኗል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ ሚኒስትሮች፣ የሥራ ኃላፊዎች፣ ተጋባዥ እንግዶችና የሃይማኖት አባቶች ተገኝተዋል፡፡

የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ በዚሁ ወቅት፤ የኢትዮጵያ ህልውናና ጥንካሬ በብዝሃነት፣ በህብረ-ብሔራዊ አንድነት ላይ የሚጸና መሆኑን አስረድተዋል።

የቀደሙ አባቶችና እናቶች አብሮነታቸውን አጎልብተው ያቆዩልንን ሀገር፣ እኛም በአንድነት ተጠናክረን ለቀጣዩ ትውልድ ለማስረከብ ቃላችንን የምናድስበት ወቅት ነው ብለዋል።

በጋራ ህልውናዋን ጠብቀንና ከፍ አድርገን ለትውልድ ማስተላለፍ የሁሉም ሃላፊነት መሆኑን አብራርተዋል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ፀጋዬ ማሞ በበኩላቸው፤ ህብር የብዙ ልዩነቶች ድምር ውጤትና የአንድነት ጥንካሬ በመሆኑ፣ አዲሱን ዓመት ስንቀበል የመደመር፣ የመደጋገፍና የፍቅር መንፈስን በማንገብ ሊሆን እንደሚገባ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ የባህሎች፣ የቋንቋዎችና የእምነቶች መኖሪያ በመሆኗ ይህ ህብረ-ብሔራዊነት የታላቅነትና የውበት ምስጥር መሆኑን ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ ያጋጠሟትን በርካታ ፈተናዎች ማለፍና ተሻጋሪ ዕቅዶችን ማሳካት የተቻለውም ልዩነቶችን ወደ ጎን በመተው በጋራ ዓላማ በመቆም ብቻ እንደሆነ አስረድተዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review