ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም የገጠሟትን ፈተናዎች ተሻግራ በአዲስ የእድገት ደረጃ ላይ ትገኛለች

You are currently viewing ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም የገጠሟትን ፈተናዎች ተሻግራ በአዲስ የእድገት ደረጃ ላይ ትገኛለች

AMN- ሐምሌ 18/2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያ በ2013 እና በ2014 ዓ.ም አካባቢ የታዩትን ፈተናዎች እና ውጣ ውረዶች በጽናት ተሻግራ፣ ዛሬ ላይ ወደ ሌላ አዲስ የእድገት እና የከፍታ ደረጃ ላይ ትገኛለች ሲሉ የሰላምና ደኅንነት ተመራማሪው ሙሉጌታ አየለ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

የሰላምና ደኅንነት ተመራማሪው ሙሉጌታ አየለ (ዶ/ር) ከኤ ኤም ኤን ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፣ የኢትዮጵያ ታሪክ እና የኢሕአፓ ጉዞ ከተለያዩ የፖለቲካ ኩነቶች አንጻር ሲመዘን፣ ይሄ ድርጅት የት ተመሰረተ? እንዴትስ ከሰመ? የሚሉ በርካታ ጥያቄዎችን ያስነሳል።

ዛሬ ላይ ቆመን ታሪክን እንደ እናቶቻችን የወንፊት ዱቄት አበጥረን ስንመረምረው፣ የኢሕአፓ ጉዞ ከሀገሪቱ ተፈጥሯዊ የእድገት መስመር እና ህዝባዊ ፍላጎት ጋር ተቃራኒ በሆነ ጎን ይቆም እንደነበር በርካታ የታሪክ አዋቂዎች ይስማሙበታል ብለዋል።

ፓርቲው በወቅቱ የነበሩትን የሀገር በቀል እውነታዎች ከመገንዘብ ይልቅ፣ የውጭ ቲዮሪዎችን በመያዝ፣ ከሀገሪቱ ተቃራኒ በመቆም “የእናት ጡት ነካሽ” የሚያስብሉ ታሪካዊ ስህተቶችን መፈጸሙንም ነው የገለጹት።

ይህ ሲባል ግን ለሀገራቸው እድገትና ለውጥ አልመው፣ እውነተኛ መስመር ይዘው የወደቁ በርካታ የተማሩ የኢትዮጵያ ውድ ልጆች አልነበሩም ማለት አለመሆኑን አስረድተዋል።

የበርካቶች ህልም ግን በቡድኑ የተሳሳተ አመራር ሳይሳካ መቅረቱን ነው ያብራሩት።

በአሁኑ ወቅት በየማዕዘኑ የምናያቸው ግጭቶች፣ ውጊያዎች እና የፖለቲካ ሹክቻዎች የራሳቸው የጀርባ ስፖንሰር፣ የገንዘብ ድጋፍ፣ የሥነ-ዘዴ እና የዓለም አቀፍ ቲዮሪ አላቸው በማለትም አክለዋል።

ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ እነዚህን ፖለቲካዊ ሴራዎች አልፋ ወደ አዲስ ምዕራፍ እየተሸጋገረች እንደምትገኝ አብራርተዋል።

በወርቅነህ አቢዮ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review