የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ዘመናዊ የላብራቶሪ ማዕከል አስመረቀ

You are currently viewing የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ዘመናዊ የላብራቶሪ ማዕከል አስመረቀ

AMN – ሐምሌ 19/2018 ዓ.ም

የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ለመከላከያ ሠራዊቱ የፅንሰ-ሀሳብ እና የተግባር የልህቀት ማዕከል በመሆን እያገለገለ እንደሚገኝ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ብርጋዴር ጄነራል ከበደ ረጋሳ ገለጹ።

ዩኒቨርሲቲው ይህንን ያለበትን የላቀ ሚና የበለጠ የሚያጎለብት የኢንጂነሪንግ እና የነርሲንግ የላቀ ላብራቶሪ ማዕከል አስመርቆ አገልግሎት ጀምሯል።

በ11 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈው ይህ አዲስ ማዕከል ለመከላከያ ሠራዊቱ ሁለንተናዊ የልህቀት ማዕከል ሆኖ የሚያገለግል መሆኑን ብርጋዴር ጄነራል ከበደ ረጋሳ ተናግረዋል።

ማዕከሉ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደራጀ ሲሆን፤ በውስጡ ሁለት የኤ.አይ (AI) ላብራቶሪዎች፣ ሁለት የሳይበር ላብራቶሪዎች እና ሁለት የ3ዲ (3D) ላብራቶሪዎችን አካቷል።

በተጨማሪም ማዕከሉ አምስት ዘመናዊ ስማርት የትምህርት ክፍሎች፣ እለታዊ እንቅስቃሴውን አስተማማኝ ለማድረግ የተገጠመ የሶላር ኃይል ሥርዓት፣ ዘመናዊ የምርምር ቦታዎች እና እጅግ ዘመናዊ መሣሪያዎች የተሟሉለት መሆኑ ተገልጿል።

በተመስገን ይመር

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review