ሁለቱም አራስ እናቶች የመጡበትን ሃገራዊ ምክክር ጉባኤ ያለምንም ችግር አሳክተው እንዲመለሱ ማረፍያ አዘጋጅተንላቸዋል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN ሐምሌ 19/2018 ዓ.ም

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ወ/ሮ ሃዳንን በአዲስ ዓለማቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ማረፍያ ክፍል በመገኘትና ለአራስ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን በማሟለት እንኳን ደስ አለሽ ብለዉ ጠይቀዋታል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ሃዳ አልማህዲ ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ለሃገራዊ ምክክር ከተፎካካሪ ፓርቲ ተወክላ የተጣለባትን ውክላና እና ሃላፊነት በታላቅ የሀገር ፍቅር እና የእኔነት ስሜት እየተወጣች እያለ ወንድ ልጅ በሰላም ተገላግላለች ብለዋል፡፡

እኛም ወ/ሮ ሃዳን በአዲስ ዓለማቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ማረፍያ ክፍል አዘጋጅተን ለአራስ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን አሟልተን እንኳን ደስ አለሽ ብለን ጠይቀናታል።

ወ/ሮ ሃዳ አልማህዲ በታሪካዊው ሀገራዊ ምክክር ወቅት ላይ የወለደችውን ወንድ ልጅ ኮሚሽን ብላ ስም አውጥታለታለች።

ወጣቷ የመጣችበትን ታላቅ ሀገራዊ ዓላማ ለማሳካት ከጥቂት ቀናት እረፍት በኋላ ወደ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤው እንደምትመለስ ነግራናለች።

ህፃን ኮሚሽንንም እደግ ተመንደግ ብለዉታል፡፡

ለሃገራዊ ምክክር ጉባኤ በተገኙበት የወለዱት ሁለቱም አራስ እናቶች የመጡበትን ሃገራዊ ምክክር ጉባኤ ያለምንም ችግር አሳክተው እንዲመለሱ ለምክክሩ በቅርበት በሚመቻቸው ቦታ ማረፍያ አዘጋጅተንላቸዋል። ሁለቱንም አራስ እናቶች ጉባኤውን አጠናቀው ወደ መጡበት እስኪመለሱ ድረስ የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ እናደርግላቸዋለን ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

እኛም ወ/ሮ ሃዳን በአዲስ ዓለማቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ማረፍያ ክፍል አዘጋጅተን ለአራስ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን አሟልተን እንኳን ደስ አለሽ ብለን ጠይቀናታል።

ወ/ሮ ሃዳ አልማህዲ በታሪካዊው ሀገራዊ ምክክር ወቅት ላይ የወለደችውን ወንድ ልጅ ኮሚሽን ብላ ስም አውጥታለታለች።

ወጣቷ የመጣችበትን ታላቅ ሀገራዊ ዓላማ ለማሳካት ከጥቂት ቀናት እረፍት በኋላ ወደ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤው እንደምትመለስ ነግራናለች።

ህፃን ኮሚሽንም እደግ ተመንደግ!

ለሃገራዊ ምክክር ጉባኤ በተገኙበት የወለዱት ሁለቱም አራስ እናቶች የመጡበትን ሃገራዊ ምክክር ጉባኤ ያለምንም ችግር አሳክተው እንዲመለሱ ለምክክሩ በቅርበት በሚመቻቸው ቦታ ማረፍያ አዘጋጅተንላቸዋል። ሁለቱንም አራስ እናቶች ጉባኤውን አጠናቀው ወደ መጡበት እስኪመለሱ ድረስ የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ እናደርግላቸዋለን።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review