AMN- ሐምሌ 22/2018 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአዘርባጃን ሪፐብሊክ ብሔራዊ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሳሂባ ጋፋሮቫ ጋር በስልክ ውይይት ማካሄዳቸውን ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ፤ ከአፈ ጉባኤ ሳሂባ ጋፋሮቫ ጋር ስትራቴጂካዊ አጋርነታችንን እና የጋራ እድገታችንን ይበልጥ በሚያሳድጉ ጉዳዮች ዙሪያ ፍሬያማና ውጤታማ ውይይት በስልክ አካሂደናል ብለዋል፡፡