ሁለተኛው ትውልድ ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራ አባላት አዲስ አበባ ገቡ

AMN- ነሐሴ 9/2018 ዓ.ም

የሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን፣ ታዳጊ ሕፃናትና ቤተሰቦቻቸውን ያካተተ የዳያስፖራ አባላት አዲስ አበባ ገብተዋል።

አባላቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዳያስፖራ አገልግሎት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

የሁለተኛ ትውልድ ዳያስፖራ አባላቱ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው የአንድ ወር ቆይታ የስፖርት ውድድር እንደሚያደርጉና የተለያዩ አካባቢዎችን እንደሚጎበኙም ተገልጿል።

ጉብኙቱ ታዳጊዎቹ የበለጠ ስለሀገራቸው እንዲገነዘቡ የሚያደርግ እንደሆነ መመላከቱን ኢዜአ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review