AMN- ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም
ሀገራችንን በግብርናው ዘርፍ ወደተሻለ የልማት ምዕራፍ ያሸጋገረ ጠንካራ መደላደል እየተፈጠረ ይገኛል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ በአማራ ክልል የምዕራብ ጎጃም ዞን ለ2019 የበጀት ዓመት ለሰፋፊ ክላስተር ተከላ የሚውል የቡና ችግኞች እንዲሁም በኩታ ገጠም የተዘራ የሰብል፣ የአትክልትና ፍራፍሬ እርሻ የዚሁ አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል።

የሀገራችንን መልከአ-ምድር የሚመጥኑና ለምግብነት የሚውሉ ተክሎችን በስፋት በመትከል የምግብ ፍላጎትን ለማሟላት፣ የአመጋገብ ስርዓትን ለማሻሻል እና ለገበያ የሚሆን ምርት ለማቅረብ የሚደረገው ጥረት በክልሉ ሁሉም ዞኖች አግሮ ኢኮሎጅን መሰረት ያደረገ ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉም አክለዋል።