AMN- ነሐሴ 14/2018ዓ.ም
አዲስ አበባ፥ በአፍሪካ ምርጥ የመንገድ መሰረተ-ልማት ካላቸው ከተሞች አንዷ መሆኗን “ግሎባል ስታስቲክስ ዋየር” ገለፀ ።
ግሎባል ስታትስቲክስ ዋየር በኤክስ ገፁ ይፋ ባደረገው መረጃ ፥ በአፍሪካ የተሻለ እና ጥራት ያለው የከተማ መንገድ መሠረተ ልማት ያላቸው ከተሞች ውስጥ አዲስ አበባን በሁለተኛ ደረጃ አስቀምጧል።
አዲስ አበባ በአጭር ጊዜ ውስጥ ጥራት ያለው የመንገድ መሠረተ-ልማት እና ሰፊ የከተማ ትራንስፎርሜሽን በማስመዝገቧ ዓለማቀፍ የስህበት ማዕከል እንድትሆን አድርጓታል።
See less