የአንጋፋዋ አርቲስት እልፍነሽ ቀኖ የአስከሬን ሽኝት መርሐ ግብር በአዲስ አበባ ስታዲየም እየተካሄደ ይገኛል

You are currently viewing የአንጋፋዋ አርቲስት እልፍነሽ ቀኖ የአስከሬን ሽኝት መርሐ ግብር በአዲስ አበባ ስታዲየም እየተካሄደ ይገኛል

AMN ጳጉሜን 3/ 2018 ዓ.ም

የአንጋፋዋ አርቲስት እልፍነሽ ቀኖ አስከሬን ሽኝት መርሐ ግብር የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፤ ቤተሰቦቿ፤ ወዳጅ ዘመዶቿ፤ አርቲስቶች፤ አድናቂዎቿ እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት በአዲስ አበባ ስታዲየም ተካሂዷል።

አንጋፋዋ አርቲስት እልፍነሽ ቀኖ ጳጉሜን 1 ቀን 2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷ የሚታወስ ሲሆን የቀብር ሥነ ሥርዓትም በአምቦ ከተማ የሚፈጸም ይሆናል።

የኦሮሞ ሴቶች የጀግንነትና የጽናት ምልክት የሆነችው እልፍነሽ ቀኖ፤ በምሥራቅ ወለጋ ዞን ነቀምቴ ከተማ አቅራቢያ በምትገኘው “ሲቡ ጉቶ” በተባለች ስፍራ በ1954 ዓ.ም ነበር የተወለደችው።

አርቲስት እልፍነሽ በ1969 ዓ.ም ወደ ትግል በመቀላቀል ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በሥነ ጥበብ ሥራዎቿ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ስታበረክት ቆይታለች።

አርቲስት እልፍነሽ ቀኖ የሁለት ሴት ልጆች እናት ነበረች።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review