AMN – ጳጉሜን 03/ 2018 ዓ.ም

አዲስ አበባ ከተማ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቋቋም በተቀመጠዉ መሥፈርት መሠረት ከአፍሪካ ቀዳሚ ከዓለም ደግሞ 2ኛ መሆኗን ኒዉዮርክ ታይምስ የተባለዉ አለም አቀፍ ጋዜጣ ዘግቧል።
ጋዜጣዉ ከቀናት በፊት ያወጣው መረጃ የብዙዎችን ትኩረት የሳበ ሲሆን አዲስ አበባ በዓለም አቀፍ ደረጃ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖን መቋቋም የምትችል ሁለተኛዋ ከተማ መሆኗን ይፋ አድርጓል።

ጋዜጣው “አልፋጂኦ” የተባለ ተቋም ከቀናት በፊት ያወጣውን ጥናት መሠረት በማድረግ ነው ዘገባውን የሰራው።
ከ22 ሚሊዮን በላይ ተከታዮች ያሉት ታዋቂው የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ እንደዘገበው፤ ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ አደጋዎችን ለመቋቋም ከሚችሉ 72 ዋና ዋና ዓለም አቀፍ ከተሞች መካከል አዲስ አበባ የተቀመጠዉን መስፈርት በማሟላት ከአፍሪካ ቀዳሚ እንዲሁም ከዓለም ደግሞ 2 ደረጃን ይዛለች።
ጥናቱ ትልልቅ የዓለም ከተሞች የአየር ንብረት ለውጥ አደጋዎች ተጋላጭነታቸውንና የመቋቋም አቅማቸውን በመገምገም ነው ደረጃውን ያወጣው፡፡
በሪፖርቱ ከአዲስ አበባ ቀድማ የተቀመጠችው የአሜሪካዋ ቺካጎ ናት፡፡
በወርቅነህ አቢዮ