ኅብር የማርሻል አርት ፌስቲቫል በዓድዋ ድል መታሰቢያ ተካሄደ

You are currently viewing ኅብር የማርሻል አርት ፌስቲቫል በዓድዋ ድል መታሰቢያ ተካሄደ

AMN- ጳጉሜን 4/2018 ዓ.ም

ጳጉሜን 4 የኅብር ቀንን ምክንያት በማድረግ “የኅብር የማርሻል አርት ፌስቲቫል” በዓድዋ ድል መታሰቢያ ተካሂዷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ባዘጋጀው ፌስቲቫል ላይ በመዲናዋ ከሚገኙ ከ13 የማርሻል አርት አይነቶች የተውጣጡ ከ50 ሺህ በላይ የማርሻል አርት ስፖርተኞች፣ አሰልጣኞች እና የስፖርቱ ቤተሰቦች ተሳትፈዋል፡፡

የዕለቱን “የኅብር ቀን” መሪ መልእክት መሰረት በማድረግ የተካሄደው ፌስቲቫል የስፖርቱ ቤተሰብ ያላቸውን የማርሻል አርት ጥበብ እና ስፖርታዊ ጨዋነት በማቀናጀት የኅብረ-ብሔራዊ አንድነትን፣ ወንድማማችነትንና የጋራ ኅብርን በተግባር ያሳዬ ነው፡፡

በዓድዋ ድል መታሰቢያ በተካሄደው ፌስቲቫል በርካታ የስፖርት አፍቃሪዎችና የከተማዋ ነዋሪዎች መታደማቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review