AMN- ጳጉሜን 4/2018 ዓ.ም
አሮጌውን ዓመት አልፎ ወደ አዲስ ዓመት መሸጋገርን የሚያበስሩ፤ የአሸንዳ፣ሻደይ፣ ሶለል፣ ጎቤ፣ ሺኖዬ ጭፈራዎች በከተማችን በታሪካዊው የአድዋ ድል መታሰቢያ በድምቀት ተከብረዋል፡፡
ኢትዮጵያ የበለፀገ የህብረተሰብ ሀብት ክምችት ያላት ሀገር ናት። የደመር መንግስትም እነዚህን ሀብቶች በመጠበቅ፣ በመንከባከብና በማልማት ለሀገር እድገትና ለህብረተሰብ ልማት ለማዋል እየሰራ ነው።
ህብረብሔራዊት በሆነችው ከተማችንም አዲስ አበባ ውብ ኢትዮጵያዊ ባህሎቻችን ጎልተው እንዲወጡ ከባህሉና እሴቱ ማግኘት የሚገባንን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጥቅም እንዲያስገኙ ትላልቅ ስራዎች እየተሰራ ይገኛል።
የህዝብ ጥንታዊ ባህልና እሴት እንዲለማ፣ እንክብካቤ እንዲደረግና ተጠብቆ ለወደፊቱ ትውልድ እንዲተላለፍ በሚያደርገው እንቅስቃሴ አወንታዊ ውጤት መገኘቱን የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡