ዓለም አቀፍ የሥራ ገበያው ያለውን ዕድል አሟጦ ለመጠቀም በትኩረት እንደሚሰራ ተገለጸ

AMN- ህዳር 3/2017 ዓ.ም

የሀገር ውስጥ የሥራ ስምሪቱን ከማስፋትና ከማዘመን በሻገር ዓለም አቀፍ የሥራ ገበያው ያለውን ዕድል አሟጦ ለመጠቀም በትኩረት እንደሚሰራ የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

ይህ የተገለፀው በ5ኛው ሀገር አቀፍ ብሔራዊ የሥራ ኤክስፖ አፈፃፀምና የቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት በተደረገበት መድረክ ላይ ነው፡፡

በመድረኩ ቀጣሪ ድርጅቶችንና የተቋማትን ውጤታማነት የሚያልቁ ሥራ ፈላጊዎችን የማገናኘቱን ሥራ አጠናክሮ ከማስቀጠል ባሻገር የሥራ ፈጠራ ስነ-ምህዳሩን ማስፋት የሚያስችሉ ጉዳዮችን በዝርዝር ተነስተዋል፡፡

በዚህም ቀጣሪ ድርጅቶችንና የተቋማትን ውጤታማነት የሚያልቁ ሥራ ፈላጊዎችን የማገናኘቱን ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተጠቁሟል፡፡

የሀገር ውስጥ የሥራ ስምሪቱን ከማስፋትና ከማዘመን በሻገር በዓለም አቀፍ ደረጃ የርቀት የሥራ መስክን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ያሉ እድሎችን አሟጦ ለመጠቀም እንደሚሰራም ተመላክቷል፡፡

በዚህም የግሉ ዘርፍ ሚናውን እንዲወጣ የማስቻል፣ ማነቆዎችን በመፍታት እና ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ዜጎችን ጥራት ያለው የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተመላክቷል፡፡

በውይይቱ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል እና የሥራ፣ ሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሰለሞን ሶካን ጨምሮ የደረጃ ዶት ኮም እና የኢትዮ ጆብስ የሥራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review