በተሰራው የኮሪደር ልማት የትራፊክ አደጋዎችን መቀነስ ተችሏል፡- የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን

AMN – ታኅሣሥ -3/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ በተሰራው የኮሪደር ልማት ባለፉት አምስት ወራት የትራፊክ አደጋዎችን መቀነስ መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን የኮርደር መሰረት ልማት ጥምር ግብረ ሀይል የ5 ወራት የኮርደር መሰረት ልማት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሂዷል።

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ክበበው ሚደቅሳ እንደገለጹት፡- በኮሪደር ልማት ስራ ለትራፊክ ፍሰት ምቹ ያልሆኑ መንገዶች እንደተስተካከሉ በማድረግ እና በተሰሩ አዳዲስ መንገዶችን ባለፉት አምስት ወራት የትራፊክ አደጋዎችን መቀነስ መቻሉን ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በበኩላቸው አዲስ አበባን ውብ፣ ለነዋሪዎቿ ምቹ እና እንደስሟ አበባ ለማድረግ በኮሪደር ልማቱ የተጣለባቸውን አደራ ለመወጣት ቀን ከለሊት እጅ ለእጅ በመያያዝ በርካታ ስራውች መሰራታቸውን ተናግረዋል፡፡

በዚህም ባለፉት በ5 ወራት ጥምር ግብረ ሃይሉ በቅንጅት በሰራው ስራ 266 ድርጅትን እና 19 ሽህ በሚሆኑ ግለሰቦችን ላይ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ በመውሰድ ከ103 ሚሊዮን ብር በላይ የማስተማሪያ ቅጣት በመቅጣት ወደ መንግስት ካዝና ገቢ መደረጉን መናገራቸውን የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል፡፡

በግምገማ መድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን፣የፅዳትና አስተዳደር ኤጀንሲ፣ የትራፊክ መኔጅመንት ባለስልጣን እና የግንባታ እና ፈቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን በቅንጅት የተሰሩ ስራዎችን በጋራ ገምግመዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review