የኢትዮጵያና የሞዛምቢክ ግንኙነት ወደ አዲስ የትብብር ምዕራፍ ተሸጋገረ

You are currently viewing የኢትዮጵያና የሞዛምቢክ ግንኙነት ወደ አዲስ የትብብር ምዕራፍ ተሸጋገረ

AMN – ሚያዝያ 19/2018 ዓ.ም

በጋራ መተማመን እና በዕድገት ርዕይ ላይ የተመሠረተው የኢትዮጵያ እና የሞዛምቢክ የሁለትዮሽ ግንኙነት፣ ዛሬ በተፈረሙ ስምምነቶች አማካኝነት ወደ አዲስ የትብብር ምዕራፍ መሸጋገሩ ተገለጸ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሞዛምቢክ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ዳንኤል ፍራንሲስኮ ቻፖ በተገኙበት በተከናወነው የፊርማ ሥነ-ሥርዓት፣ ሀገራቱ በበርካታ ቁልፍ መስኮች በጋራ ለመሥራት የሚያስችሏቸውን የመግባቢያ ሰነዶች ተፈራርመዋል።

ከስምምነቶቹ መካከልም በወታደራዊ ሥልጠና፣ በጤና፣ በቱሪዝም እና በሲቪል አቪዬሽን ዘርፎች ትብብር ለማድረግ የሚያስችሉ ጉዳዮች በዋናነት ተካተዋል።

በተለይም ደግሞ የከተማ ልማትና የቤት ግንባታን ጨምሮ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን፣ በዲጂታል መታወቂያ እና በዲጂታል የሕዝብ መሠረተ ልማት ግንባታ ዙሪያ በቅርበት ለመሥራት ስምምነት ላይ ተደርሷል።

እነዚህ ሰነዶች ከተራ የፖሊሲ ሰነድነት ባለፈ ለሁለቱ ሀገራት የጋራ ብልጽግና ተጨባጭ መንገዶችን የሚቀይሱ መሆናቸው በወቅቱ ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በከፍተኛ ደረጃ እያደገ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ሀገራችን የደረሰችበትን ልምድና እውቀት ለአፍሪካውያን ወንድሞቿ ለማካፈል ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጣለች።

በመሆኑም ይህ አጋርነት ኢትዮጵያና ሞዛምቢክ እርስ በእርስ ለመማማር

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review