ኢትዮጵያ እና ሳኡዲ አረቢያ በሁለቲዮሽ እና በቀጣናዊ ሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ላይ መከሩ

You are currently viewing ኢትዮጵያ እና ሳኡዲ አረቢያ በሁለቲዮሽ እና በቀጣናዊ ሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ላይ መከሩ

AMN ግንቦት 10/2018 ዓ.ም

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) የሳውዲ ዓረቢያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢንጂነር ዋሊድ ኤል ኬሬጂን በጽ/ቤታቸዉ ተቀብለው አነጋገሩ።

በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ባተኮረው ውይይታቸው፥ ኢትዮጵያና ሳውዲ ዓረቢያ በጠንካራ የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር ላይ የተመሰረተ የረጅም ጊዜ ታሪካዊ ግንኙነት እንዳላቸው ዶ/ር ጌዲዮን አስታውቀዋል።

ሁለቱ አገራት በብዙ የጋራ ጉዳዮች ላይ ተመሳሳይ አቋም እንዳላቸው የጠቀሱት ሚኒስትሩ ይህንንም አጠናክሮ መቀጠል ይገባል ብለዋል።

ዶ/ር ጌዲዮን በውውይቱ ወቅት አፅንኦት ከሰጡት ጉዳይ አንዱ በሳኡዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊን ድህንነት የማስጠበቅ ጉዳይ ሲሆን ፥ ህጋዊ የስራ ስምሪት እድሎች እንዲሰፉ ማድረግ ወሳኝ መሆኑን አስረድተዋል።

የሳኡዲ አረቢያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢንጂነር ዋሊድ ኤል ኬሬጂ በበኩላቸው ሳውዲ ዓረቢያ ከኢትዮጵያ ጋር ላላት ታሪካዊ ግንኙነት ትልቅ ቦታ እንደምትሰጥ ተናግረዋል።

ህጋዊትን የተከተለ የስራ ስምሪት በሳኡዲ አረቢያ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች ደህንነትን መረጋገጥ ቁልፍ ጉዳይ መሆኑንም ምክትል ሚኒስትሩ ጨምረው ገልፀዋል።

ሁለቱ ወገኖች በቀጠናዊ ሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ላይ የመከሩ ሲሆን ፥ በአካባቢው ለሚስተዋሉ ግጭቶች ፓለቲካዊ መፍትሄ ማፈላለግ ውይይት ብቸኛው አስተማማኝና ዘላቂ መንገድ መሆኑንም መጥቀሳቸዉን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review