AMN ሚያዝያ 21/2018 ዓ.ም
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት የከተማ አስተዳደራችን ተቋማት ሰው ላይ የተንጠለጠሉ ሳይሆኑ ቀጣይነት ያላቸው በሲስተም የሚመሩ ጠንካራ ተቋማት የማድረግ ስራ ፍሬው እየታየ ነው ብለዋል፡፡
ዛሬ ጠዋት በደንብ ማስከበር ባለስልጣን የተሰሩ የተቋም ሪፎርም ስራዎችን ጎብኝተናል። ከዚህ በፊት ነዋሪዎች ቅሬታቸውን “ወይ ሀምሳ ወይ አንሳ” የሚል ቅፅል ስም አውጥተውለት እንደነበር አይዘነጋም ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ይህንን ስም ለመለወጥ እና የነዋሪዎችን እርካታ ለማሳደግ በተከታታይ በተሰራ ሪፎርም በአስተሳሰብ፣ በስነ ምግባር እንዲሁም የዘመነ አሰራር በመተግበር መሰረታዊ ለውጥ አስመዝግቧል ።
ከወረቀት ንክኪ ነፃ፣ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት፣ መረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ለመስጠት እና ቅሬታዎችንም ለመፍታት የሚያግዙ እንዲሁም የደንብ ጥሰትንም በቀላሉ በመለየት ለማረም የሚስችሉ ናቸው ።

በተጨማሪም የዜጎች ቀጥታ ተሳትፎ መተግበሪያ፣ በ5 ቋንቋ አገልግሎት የሚሰጥ የጥቆማና ቅሬታ ማቅረቢያ ዘመናዊ የጥሪ ማዕከል (calling center)፣ የሁኔታዎች መከታተያ ክፍል (situation room)፣ ዘመናዊ የስልጠና ማዕከል (Smart training center)፣ ዘመናዊ የቢሮ አደረጃጀት (Smart office)፣ የህፃናት ማቆያ፣ የሰራተኛ ካፍቴሪያ፣ የሸማች ሱቅ፣ የሰፖርት ማዕከል (ጂምናዚየም) ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል።
በመጨረሻም በትጋት መሰረታዊ ለወጥ ያስመዘገቡትን የተቋሙን አመራሮች እና የኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ቢሯችንን ከልብ አመሰግናለሁ ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡