የረጲ የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ የከተማዋ የአረንጓዴ ዐሻራ ተስፋዎች ማሳያ መሆን ይችላል

You are currently viewing የረጲ የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ የከተማዋ የአረንጓዴ ዐሻራ ተስፋዎች ማሳያ መሆን ይችላል

AMN- ሰኔ 28/2018 ዓ.ም

የረጲ የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ የከተማዋ የአረንጓዴ ዐሻራ ተስፋዎች ማሳያ መሆን እንደሚችል በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ገለፁ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ሰራተኞች እና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች በረጲ የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ስፍራ የችግኝ ተከላ መርኃ ግብር አካሂደዋል።

በዚሁ ወቅት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ፤ የረጲ የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ስፍራ በርካታ ችግሮች እንደነበሩት አንስተዋል፡፡

በተከታታይ በስፍራው የተተከሉ ችግኞች አሁን ላይ ለከተማዋ የአረንጓዴ ዐሻራ ፍሬዎች ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

የአረንጓዴ ዐሻራ ኢንሼቲቭ እንዲሳካ የማህበረሰቡ ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የገለጹት ደግሞ የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሌሊሴ ነሜ (ዶ/ር) ናቸው፡፡

የመርኃ ግብሩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው፤ አዲስ አበባን ውብ እና ጽዱ የማድረግ ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል፡፡

በአረንጓዴ ዐሻራ መርኃ ግብር የተራቆቱ መሬቶችን መልሶ ለማልማት፣ የሀገሪቱን የደን ሽፋን ለማሳደግ እና የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም በኢትዮጵያ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑ ይታወቃል።

በዳንኤል መላኩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review