ብልፅግና የሕዝብ የለውጥ ፍላጎት የወለደውና ቃሉን በተግባር የገለጠ ፓርቲ መሆኑን ባሕርዳር ማሳያ ሆናለች – አቶ ጎሹ እንዳላማው

You are currently viewing ብልፅግና የሕዝብ የለውጥ ፍላጎት የወለደውና ቃሉን በተግባር የገለጠ ፓርቲ መሆኑን ባሕርዳር ማሳያ ሆናለች – አቶ ጎሹ እንዳላማው

AMN ግንቦት 18/2018

ብልፅግና የሕዝብ የለውጥ ፍላጎት የወለደውና ቃሉን በተግባር የገለጠ ፓርቲ መሆኑን ባሕርዳር ማሳያ ሆናለች ሲሉ የባህር ዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ገለጹ።

የብልፅግና ፓርቲ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር በሚል መሪ ሀሳብ የምረጡኝ ቅስቀሳ ማጠቃለያና ሕዝባዋ የድጋፍ ሰልፍ በባሕርዳር ከተማ እያካሄደ ይገኛል፡፡

በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ በተገኘበት የድጋፍ ሰልፍ ላይ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንትና የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እና የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ አረጋ ከበደን ሌሎች የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ የፓርቲው እጩዎች እንዲሁም በርካታ አባላትና ደጋፊዎች ተገኝተዋል።

የባህር ዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማው፣ ብልፅግና ፓርቲ የህዝብን የለውጥ ፍላጎት ተከትሎ የተመሠረተና ሀገርን ወደ አዲስ የለውጥ ምዕራፍ ያሸጋገረ የሕዝብ ፓርቲ መሆኑን ገልጸዋል።

ፓርቲው ባለፉት ጥቂት ዓመታት የገባውን ቃል በተግባር በመተርጎም ተጨባጭ ለውጦችን ማስመዝገቡንና ለዚህም የባህርዳር ከተማ የውበት፣ የሰላምና የልማት ጉዞ በቂ ማሳያ መሆኑን አብራርተዋል።

በከተማዋ የተከናወኑትን ዘመናዊ የአስፋልትና የጣና ዳርና የኮሪደር ልማት ስራዎች፣ የብስክሌትና የእግር መንገድ ግንባታዎችን፣ የትራንስፖርትና የፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ ማሻሻያዎችን እንዲሁም የባህር ዳር ስታዲየም ግንባታ ማጠናቀቂያ ስራዎችን በዝርዝር አቅርበዋል።

ብልፅግና ፓርቲ በሀሳብ የበላይነት እንደሚያምን የጠቆሙት አቶ ጎሹ፤ የክልሉንና የከተማዋን ሁለንተናዊ እድገት ለማስቀጠል እንደሚሠራ መናገራቸዉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review