አሜሪካ ማደያዎችና ጀልባዎችን ኢላማ ያደረገ አዲስ ጥቃት በኢራን ላይ ሰነዘረች

You are currently viewing አሜሪካ ማደያዎችና ጀልባዎችን ኢላማ ያደረገ አዲስ ጥቃት በኢራን ላይ ሰነዘረች

AMN ግንቦት 18/2018 ዓ.ም

ዩናይትድ ስቴትስ በደቡባዊ ኢራን ላይ አዲስ ጥቃት መፈጸሟን ገልጻለች:: ጥቃቱ የኢራንን ማደያዎች እና ፈንጂዎችን ለማጥመድ ይንቀሳቀሱ የነበሩ ጀልባዎችን ኢላማ ያደረገ ነው ብላለች፡፡

ጥቃቶቹ የተፈጸሙት ከኢራን ኃይሎች ሊሰነዘሩ የሚችሉ ጥቃቶችን ለመከላከል እንደሆነ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ኢራን እስካሁን ድረስ ከአሜሪካ ለተሰነዘረባት ጥቃት ምላሽ አልሰጠችም፡፡

ይሁን እንጂ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እስማኢል ባቃኢ ቀደም ብለው እንደተናገሩት፥ ጦርነቱን ለማቆም በሚደረገው ንግግር ላይ የተወሰነ መሻሻል ቢታይም እስካሁን ድረስ ስምምነት ላይ መድረስ አልተቻለም፡፡

በወንድማገኝ አሰፋ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review