AMN ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ/ም

1447ኛው የኢድ አል አድሀ (አረፋ) በዓልን ምክንያት በማድረግ ሶላት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡
በዚህ መሰረት፦
ከመገናኛ በ22 አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ ቅ/ዑራኤል አደባባይ
ከቦሌ በአትላስ መብራት ወደ ቅ/ዑራኤል አደባባይ አትላስ እና ፒኮኪ መብራት
በቦሌ መንገድ ወደ መስቀል አደባባ ኦሎምፒያ አደባባይ
ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ መብራት አጎና ሲኒማ መስቀለኛ
ከቡልጋሪያ መብራት ወደ ገነት ሆቴል ሜክሲኮ አደባባይ ቡልጋሪያ መብራት ላይ
ከልደታ ፀጠል ወደ ሜክሲኮ አደባባይ AU ሚካኤል መታጠፊያ
ከጦር ኃይሎች ወደ ሜክሲኮ አደባባይ ከፍተኛ ፍ/ቤት
ከአብነት አካባቢ ወደ ጨፌ ሜዳ መብራት ፈረሰኛ መብራት
ከሞላ ማሩ መስቀለኛ ወደ ጌጃ ሰፈር መውረጃ ሞላ ማሩ መታጠፊያ
ከመርካቶ አካባቢ ወደ ጥቁር አንበሳ ተክለ ሃይማኖት አደባባይ
ከፒያሳ ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ ባንኮድሮማ መብራት
ከሲግናል ወደ ካዛንቺስ ሴቶች አደባባይ ላይ የሚሄዱ ከንጋቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።
ከበዓሉ ዋዜማ ምሽት ጀምሮ ከላይ በተጠቀሱት ቦታዎች ላይ ተሽከርካሪዎችን ለአጭርም ይሁን ለረጅም ሠዓት ማቆም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ለኤኤምኤን በላከዉ መረጃ አስታውቋል፡፡