AMN – ግንቦት 19/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዛሬ አመሻሹን በቄራ አልማዝዬ ሜዳ ጉብኝት አድርገዋል።
ከዚህ በፊት በአዲስ መልክ ተገንብቶ ለአገልግሎት ክፍት ተደርጎ የነበረው እና በቄራ አካባቢ የሚገኘው ስመ ጥሩ አልማዝዬ ሜዳ የተሰራበትን አግባብና ደረጃውን እና ስሙን የማይመጥን በመሆኑ በከንቲባ አዳነች አቤቤ አስተባባሪነትና በባለሀብቶች ተሳትፎ ከፍ ባለ ደረጃ እድሳት እየተደረገለት ይገኛል።

ማምሻውን ይህንኑ ስራ ለመጎብኘት የተገኙት ከንቲባ አዳነች፤ በአካባቢው ወጣቶችና በመላው ነዋሪ ሞቅ ያለ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
የአካባቢው ስፖርት ቤተሰብና ተፅኖ ፈጣሪ ወጣቶች ክብርት ከንቲባ ለሰጡት ትኩረትና አመራር እንዲሁም በጉብኝቱ የተሰማቸውን ደስታ መግለጻቸውን የኢዲስ አበባ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል።