AMN – ግንቦት 24/2018 ዓ.ም
7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ በተሳካ ሁኔታ እንደሚካሄድ ያላቸውን ተስፋ የአፍሪካ ሕብረት የታዛቢ ቡድን መሪ ኡሁሩ ኬንያታ ገልጸዋል፡፡
የአፍሪካ ኅብረት ታዛቢ ቡድን መሪ የሆኑት የኬንያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የምርጫ ዝግጅትን በየምርጫ ጣቢያዎች ተዘዋውረው እየጎበኙ ይገኛሉ።
በጉብኝታቸው በሰጡት አስተያየት ኢትዮጵያ የአፍሪካ መዲና እንደመሆኗ ፣ የኢትዮጵያ ስኬት ለመላ አፍሪካ በጎ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ጠቅሰዋል፡፡
የድምጽ አሰጣጡ በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄድ ምኞታቸው መሆኑንና ይህም እንደሚሆን ተስፋ እንዳላቸው በጉብኝታቸው ወቅት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል፡፡