ጠቅላላ ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ አሳታፊና የኢትዮጵያን አሸናፊነት ያበሰረ ነው-የጋራ ምክር ቤቱ

You are currently viewing ጠቅላላ ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ አሳታፊና የኢትዮጵያን አሸናፊነት ያበሰረ ነው-የጋራ ምክር ቤቱ

AMN ግንቦት 27 /2018

ሰባተኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ አሳታፊና የኢትዮጵያን አሸናፊነት ያበሰረ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አስታወቀ።

የኦሮሚያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ በማካሄድ ባወጠው የአቋም መግለጫ፤ ምርጫው ሰላማዊ፣ዴሞክራሲያዊና አሳታፊ ሆኖ መካሄዱን ገልጸዋል።

የጋራ ምክር ቤቱ ጸሐፊ አቶ ታሪኩ ድንበሩ የአቋም መግለጫውን ባቀረቡበት ወቅት እንዳሉት፤ የዘንድሮው ምርጫ ከቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ እጅግ የተሻለ ሂደት የታየበት ነበር።

የምርጫው ሂደትም ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ህዝቡ በነጻነት ድምፅ የሰጠበት መሆኑን ገልጸዋል።

የኦሮሚያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ አሳታፊና ኢትዮጵያን አሸናፊ ያደረገ ታሪካዊና ሰላማዊ ሂደት መሆኑን ተናግረዋል።

በድምጽ መስጫው ዕለት መላው የክልሉ ህዝብ ከማለዳ ጀምሮ እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ በትዕግስት ተሰልፎ ድምጹን በመስጠት ያሳየው ጽናትና ቁርጠኝነት በእጅጉ የሚደነቅ መሆኑን አንስተዋል።

በኦሮሚያ ክልል ምርጫው በስኬትና በሰላም እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ ዜጎች፣የጸጥታ አካላት፣ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሲቪክ ማኅበራትና ምርጫ አስፈጻሚዎች ምስጋናውን አቅርቧል።

የጋራ ምክር ቤቱም በጠቅላላው የምርጫ ሂደት ውስጥ በትኩረት በመንቀሳቀስ የራሱን ድርሻ መወጣቱን በአቋም መግለጫቸው አረጋግጠዋል።

ምርጫው በሰላማዊ፣በዴሞክራሲያዊ እና ስኬታማ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅ የጋራ ምክር ቤቱ በትብብርና በቁርጠኝነት ሲሰራ መቆየቱን ገልጸዋል።

በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫም ኢትዮጵያዊያን ከዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ውጭ የስልጣን ባለቤት መሆን እንደማይቻል በተግባር ማሳየታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review