ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ ክልል ምክር ቤቶች መቀላቀል መጀመራቸው በዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ሂደት አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ነው

You are currently viewing ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ ክልል ምክር ቤቶች መቀላቀል መጀመራቸው በዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ሂደት አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ነው

AMN- ሰኔ 16/2018 ዓ.ም

በኢትዮጵያ በተካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ ክልል ምክር ቤቶች መቀላቀል መጀመራቸው በዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ሂደት ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የከፈተና ተስፋ ሰጪ ገጽታዎችን የያዘ ነው።

ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በክልል ምክር ቤቶች መቀላቀል የሕዝብን የተለያዩ ድምጾች እና ፍላጎቶች በአስተዳደር እርከን ላይ እንዲንጸባረቁ ከማድረግ ባሻገር የፖለቲካ መሪዎች በምክር ቤቶች ውስጥ ልምድ እንዲቀስሙ ያደርጋል።

ለአብነትም በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለአዲስ አበባ ምክር ቤት መቀመጫ ካገኙት ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል፤ ብልፅግና ፓርቲ 134፣ ኢዜማ 8፣ አንድ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ 4፣ ሕዳሴ ፓርቲ 2፣ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር 2፣ ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት 2 ፣ ሰላም ለኢትዮጵያ ጥምረት 2፣ የወላይታ ሕዝቦች ንቅናቄ 1፣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ 1፣ የወሎ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ 1፣ ዳንኤል ጌታቸው ጋረደው የግል እጩ 1 የመቀመጫ ውጤት ያገኙት ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ይሄም በአንድ ወገን ብቻ የሚወሰኑ ፖሊሲዎችን በማስቀረት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ውይይት እንዲካሄደ እና ሰላማዊ የሃሳብ ውድድር እንዲኖር ያስችላል።

የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ድምጽ በምክር ቤቶች እንዲሰማ እና በፖለቲካዊ ሥርዓት ውስጥም ያላቸው የመተማመን ስሜት እንዲጨምር የሚያደርግ ይሆናል፡፡

በዚህም የምክር ቤቶች መሠረታዊ ተግባር አስፈጻሚውን አካል መቆጣጠር በመሆኑ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ ክልል ምክር ቤቶች መግባት ይህንን ሚና እንደሚያጠናክርም ይታመናል፡፡

እንዲሁም ውሳኔዎች በሚወሰኑበት ወቅት በተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሰላማዊ የሃሳብ ውድድሮች እና አማራጭ ሃሳቦች መነሳታቸው የአስተዳደር ሥራዎች ይበልጥ ግልጽ እና ተጠያቂነት የተሞላባቸው እንዲሆኑ ያደርጋል።

ይህ ለውጥ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ልዩነት በኃይል ከመፍታት የሚያላቅቅ እና ወደ ሰላማዊ የሃሳብ ውድድር የሚያሸጋግር ነው፡፡

ፓርቲዎች በምክር ቤት ውስጥ በጋራ በመስራት፣ አብሮ የመኖር እና ሰላማዊ የሃሳብ ውድድር ባህልን እንዲያዳብሩ ከማድረግ ባለፈ ለኢትዮጵያ የወደፊት የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ዋና መሠረት ነው።

ወደ ክልል ምክር ቤቶች የሚቀላቀሉ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተለያየ አስተሳሰብ ያላቸው በመሆኑ ተቋማት የሕዝብን ጥያቄ ለመመለስ የተሻለ አቅም እንዲኖራቸውም የሚያደርጉ ሲሆን አሰራሮችንም ያሻሽላሉ፡፡

ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ ክልል ምክር ቤቶቹ መቀላቀል መጀመር በምርጫ ሂደትና በወደፊት የኢትዮጵያ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ላይ የሕዝቡ ተሳትፎ እንዲጨምርም ያበረታታሉ።

በአጠቃላይ ይህ እርምጃ ኢትዮጵያ ወደ ሁሉን አቀፍ እና አሳታፊ ወደ ሆነ የዲሞክራሲ ጉዞ እያመራች መሆኗን የሚያሳይ ትልቅ ምዕራፍ ነው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ ባደረገው ውጤት መሠረት፤ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላማዊና በዲሞክራሲያዊ መንገድ ተጠናቆ የብልፅግና ፓርቲ አብላጫ ድምፅ በማግኘት ማሸነፉን አስታውቋል።

ምርጫው የኢትዮጵያን የፖለቲካ ብስለት እንዲሁም የሕዝብን የሉዓላዊነት ስልጣን ያረጋገጠ ታሪካዊ መድረክ መሆኑን በርካቶች እየገለጹ ነው፡፡

ታሪካዊው ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅና የዲሞክራሲ ባህል እንዲጎለብት በውድድሩ የተሳተፉ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉልህ ሚና አበርክተዋል፡፡

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ነፃ፣ ፍትሃዊና ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ የተካሄደ በመሆኑ የምርጫውን ውጤት አክብረው እንደሚቀበሉም የተለያዩ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች እየገለጹ ይገኛል፡፡

የሻምበል ምህረት

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review