የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች እያስመረቀ ነው

You are currently viewing የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች እያስመረቀ ነው

AMN ሰኔ 18/2018 ዓ.ም

አንጋፋው የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን 4 ሺህ 83 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው፡፡

ዩኒቨርሲቲው በቅድመ ምረቃ፣ በድኅረ ምረቃ፣ በሰብስፔሻሊቲ እና በሶሥተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 4 ሺህ 83 ተማሪዎችን ሲሆን እያስመረቀ የሚገኘው ለስምንት አንጋፋ ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በምረቃ ፕሮግራሙ ዩኒቨርሲቲው ለታዋቂው የሰው ዘር ጥናት ምሁር ፕሮፌሰር ዶናልድ ካርል ጁሀንሰን የክብር የሳይንስ ዶክትሬት ዲግሪ እንደሚሰጥ አስታውቋል፡፡

ፕሮፌሰሩ በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር 1974 በአፋር ክልል “ሉሲ” ወይም “ድንቅነሽ” በመባል የምትታወቀውን የ3 ነጥብ 2 ሚሊየን አመት እድሜ ያላት የሰው ዘር ቅሪት አካል በማግኘታቸው የሚታወቁ ምሁር ናቸው፡፡

በተጨማሪም በሙያቸውና በኃላፊነታቸው ለዩኒቨርሲቲው ስኬት በዓመቱ የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ የፕሬዚዳንሻል ሽልማት እንደሚበረከትላቻው ለማወቅ ተችሏል፡፡

በሸዋዬ ከፍያለው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review