AMN- ሰኔ 22/2018 ዓ.ም
በመዲናዋ በ2018 ዓ.ም የስምንተኛ ክፍል ከተማ አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 95.85 በመቶ የሚሆኑት ወደ ቀጣዩ ክፍል መሸጋገራቸውን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።
የፈተና ውጤቱን ይፋ መደረግ አስመልክቶ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) መግለጫ ሰጥተዋል።
ኃላፊው በመግለጫቸው፤ በትምህርት ዘመኑ 85 ሺህ 737 ተማሪዎች የስምንተኛ ክፍል ከተማ አቀፍ መልቀቂያ ፈተናውን መውሰዳቸውን በመጥቀስ፣ 82 ሺህ 193 የሚሆኑት 50 እና ከዛ በላይ አምጥተው አልፈዋል ብለዋል፡፡

ፈተናው ከተሰጠባቸው 669 ትምህርት ቤቶች መካከል 441 ትምህርት ቤቶች መቶ ፕርሰት ወደ ቀጣዩ የክፍል ደረጃ ተማሪዎቸን ማሸጋገራቸውም በመግለጫው ተመላክቷል።
የቢሮ ኃላፊው ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ከተማ አስተዳደሩ ለትምህርት ዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራ መቆየቱን በመግለጽ፣ ይህም ለውጤቱ መገኘት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ተናግረዋል።
በራሄል አበበ