ከንቲባ አዳነች አቤቤ የእንጦጦ – ቀበና የወንዝና የወንዝ ዳርቻ ልማት በስኬት እንዲጠናቀቅ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር ደማቅ አሻራቸዉን ያኖሩ አካላትን አመሰገኑ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ የእንጦጦ – ቀበና የወንዝና የወንዝ ዳርቻ ልማት በስኬት እንዲጠናቀቅ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር ደማቅ አሻራቸዉን ያኖሩ አካላትን አመሰገኑ

AMN ሰኔ 22 /2018 ዓ.ም

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የእንጦጦ – ቀበና የወንዝና የወንዝ ዳርቻ ልማት በስኬት እንዲጠናቀቅ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር ደማቅ አሻራቸዉን ያኖሩ አካላትን አመስግነዋል፡፡

ከንቲባዋ ዛሬ የምስጋና ቀን ነዉ በሚል መሪ ሃሳብ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት የእንጦጦ – ቀበና የወንዝና የወንዝ ዳርቻ ልማት በስኬት እንዲህ ባማረ መልኩ ለማጠናቀቅ፤ ለመጪው ትውልድ የሚተላለፍ ደማቅ አሻራ እንድናኖር አብራችሁን የሰራችሁ የመሰረተ ልማት ተቋሞቻችን አመራሮች፣ ሰራተኞች፣ ኮንትራክተሮች፥ አማካሪዎች፣ የቀን ሰራተኞች፣ ባለሙያዎች፣ የአካባቢው ነዋሪዎች ታላቅ አክብሮትና ምስጋናችን ይድረሳችሁ ብለዋል።

ያለማቋረጥ እንደዚህ ያሉ አዳዲስ ሜጋ ፕሮጀክቶችን ሰርተን ለትውልድ ስጦታ አድርገን ስናቀርብ በከተማችን በጀት እንጂ በብድር ወይም በእርዳታ አይደለም ያሉት ከንቲባ አዳነች፣ በመሆኑም የከተማችን ግብር ከፋዮች፣ የገቢ ሰብሳቢና የፋይናንስ ተቋሞቻችን አንድ ላይ ተደምረን በትብብር ያሳካነው ልማት በመሆኑ ሁላችሁንም በከተማችን ነዋሪዎች፣ በአስተዳደራችን እና በራሴ ስም ከልብ አመሰግናለሁ ብለዋል።

የከተማችን ነዋሪዎችን እንኳን ደስ አላችሁ እያልኩ፣ ይህንን እጅግ ውብና ማራኪ የመዝናኛና ጤና መጠበቂያ ሆኖ የተጠናቀቀ የቀበና ወንዝ እና የወንዝ ዳርቻ ልማት በዋናነት የተሰራው ለእናንተ ነውና መጥታችሁ እንድትጎበኙ፣ እንድትዝናኑ እጋብዛችኋለሁ ሲሉም ከንቲባ አዳነች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ልማቱንም በዘላቂነት ለትውልድ እንዲተላለፍ እንድትንከባከቡት እና እየጠበቃችሁ እድትጠቀሙበት እደራ እላለሁ ብለዋል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመልዕክታቸው።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review