የትዉልድ ድምጽ የሆነዉ የኤኤምኤን “አሸናፊ ትውልድ” የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር ዛሬ ይካሄዳል

You are currently viewing የትዉልድ ድምጽ የሆነዉ የኤኤምኤን “አሸናፊ ትውልድ” የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር ዛሬ ይካሄዳል

AMN – ሰኔ 28/2018 ዓ.ም

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ከአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የ“አሸናፊ ትውልድ” የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡

የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድሩ “አሸናፊ ትውልድ” በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄድ ሲሆን፤ የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ አመራሮች እና ሰራተኞችን ጨምሮ እስከ 5 ሺህ የሚደርሱ ወጣቶችና የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ይሳተፉበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የሩጫ ውድድር መርሃ ግብሩ መነሻውን ዓድዋ ድል መታሰቢያ አድርጎ አዲስ ከተሰራው የቀበና ወንዝ ዳርቻ ልማት ላይ የሚጠናቀቅ ነው፡፡

ይሄም የህዝብ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ያለመ ሲሆን የስፖርት ቱሪዝምን ከማነቃቃት አኳያም ጉልህ ሚና ይጫወታል፡፡

የሩጫ ውድድሩ ማህበራዊ ትስስር፣ እህትማማችነትና ወንድማማችነት እንዲሁም አብሮነት ተግባራዊ የሚደረግበት ሲሆን የአስተሳሰብና የስብዕና ግንባታም ከፍ እያለ መምጣቱ በተጨባጭ የሚረጋገጥበት ነው፡፡

በሻምበል ምህረት

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review