በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ለነዋሪዎቻችን ፍቅርና ክብር ከሰጠንበት ስራዎች አንዱ የሆነውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ፕሮግራማችን ዛሬ 30ኛውን ማዕከል ገንብተን ስራ አስጀምረናል- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ለነዋሪዎቻችን ፍቅርና ክብር ከሰጠንበት ስራዎች አንዱ የሆነውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ፕሮግራማችን ዛሬ 30ኛውን ማዕከል ገንብተን ስራ አስጀምረናል- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN- ሰኔ 28/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ከመመገብ ባሻገር በማለት ባስተላለፉት መልእክት፤ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ከመመገብ ባሻገር ማህበራዊ ፍትህን የምናነግስበት እና ለነዋሪዎቻችን ፍቅርና ክብር ከሰጠንበት ስራዎች አንዱ የሆነውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ፕሮግራማችን ዛሬ 30ኛውን ማዕከል ገንብተን ስራ አስጀምረናል ብለዋል።

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ 4ኛ ቅርንጫፍ የሆነው ይህ 30ኛው የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ከቂርቆስ፣ ከሸራተን ማስፋፊያ እና ከካሳንቺስ አካባቢ ህጋዊ ቤት ሳይኖራቸው በጥገኝነትና በደባልነት ይኖሩ የነበሩ አቅመ ደካሞች፣ ምንም ቋሚ ገቢ ያልነበራቸው፣ አራብሳ ቤት ሰርተን ያስገባናቸው አረጋውያን እና ለተለያዩ ማህበራዊ ችግር የተጋለጡ ነዋሪዎቻችን የሚኖሩበት አካባቢ በመሆኑ የምገባ ማዕከል በመጀመር ጊዜያዊ ችግራቸውን በማቃለልና በዘላቂነት ቋሚ የሥራ እድል እንዲያገኙ የሚያስችል ስራም የጀመርንበት ማዕከል ነው ብለዋል።

በከተማችን የገነባናቸው የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከላት ሰው ተኮርነታችን በተግባር የሚገለጥባቸው፣ ጊዜያዊ ችግሮችን የምንፈታባቸው ሲሆኑ በዘላቂነት ደግሞ ሌት ተቀን በመስራት ሃገራችንን ለማበልፀግ ግባችንን ለማሳካት እንተጋለን ሲሉም ገልጸዋል፡፡

በከተማችን ማህበራዊ ሃላፊነትን መወጣት እያደገ የመጣ ሲሆን፤ ዛሬም ካላችሁ በማካፈል አብራችሁን የሰራችሁ እንዲሁም በማዕከሉ በቋሚነት ለመመገብ ቃል የገባችሁ በጎ አድራጊዎችን በተጠቃሚ ነዋሪዎቻችን፣ በከተማ አስተዳደራችንና በራሴ ስም አመሰግናለሁም ብለዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review