ምክር ቤቱ ያጸደቃቸው አጀንዳዎች:-
1. የምክር ቤቱን 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፤
2. የከተማ አስተዳደሩን የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2019 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፤
3. የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የ5 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፤
4. የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት 2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም እና የኦዲት ሪፖርት ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፤

5. የአዲስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፤
6. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2019 በጀት አዋጅ ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፤
7. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ማስለቀቅና ካሳ ጉዳዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ እንደገና ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፤ – ከንቲባ አዳነች አቤቤ