የአየር ማረፊያው ለአገልግሎት መብቃት የአካባቢውን የንግድ፣ የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ የሚያነቃቃ ነው-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

You are currently viewing የአየር ማረፊያው ለአገልግሎት መብቃት የአካባቢውን የንግድ፣ የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ የሚያነቃቃ ነው-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

AMN ሐምሌ 5 /2018

የአየር ማረፊያው ለአገልግሎት መብቃትም የአካባቢውን የንግድ፣የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ በማነቃቃት፣ ለሀገራችን የኢኮኖሚ ዕድገት አዲስ ምዕራፍ እንደሚከፍት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አስገንዝበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአዲስ መልክ ተሻሽሎ ደረጃው ከፍ ብሎ የተገነባውን የደብረ ማርቆስ ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት አውሮፕላን ማረፊያ ዛሬ በይፋ መርቀዋል።

በ2 ሺህ 400 ሜትር ርዝመትና በ30 ሜትር ስፋት የተገነባው አውሮፕላን ማረፊያው፣ እንደ Q400 እና ቦይንግ 737 ያሉ ግዙፍ የሕዝብና የጭነት አውሮፕላኖችን ማስተናገድ የሚያስችል አቅም አለው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ እንደገለጹት፤ የአውሮፕላን ማረፊያው ተመርቆ ሥራ መጀመሩ የደብረ ማርቆስ ከተማ ነዋሪዎችን የዘመናት ጥያቄ የመለሰ ነው።

የአየር ማረፊያው ለአገልግሎት መብቃትም የአካባቢውን የንግድ፣ የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ በማነቃቃት፣ ለሀገራችን የኢኮኖሚ ዕድገት አዲስ ምዕራፍ እንደሚከፍት አስገንዝበዋል።

የአውሮፕላን ትራንስፖርት መጀመሩ እንዳለ ሆኖ በየብስ ትራንስፖርት የመንቀሳቀስ ጉዳይም በጋራ ጥረት ወደ ተሟላ ሁኔታ መመለስ እንዳለበት ገልጸዋል።

የአየር ትራንስፖርት መጀመሩ በቀን ሦስት ጊዜ በረራ በማድረግ ምቾት የሚፈጥር ቢሆንም፣ የየብስ ትራንስፖርትን መጠቀም ለሚፈልጉ ዜጎች ሰላም በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።

መንግሥት ለውይይትና ለንግግር ለሚፈልግ ለማንኛውም አካል በሩ ክፍት መሆኑን በመግለጽ፤ የማያስማሙ ጉዳዮች ካሉ በሰላማዊና በሰለጠነ የፖለቲካ አግባብ መፍታት እንደሚቻል ጥሪ አቅርበዋል።

ልማት በባህሪው ጊዜን፣ትብብርንና ጥበቃን እንደሚፈልግ ያስረዱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ የጎደለውን ልማት፣ብልፅግና፣መተማመንና መከባበር ለመሙላትና ለልጆቻችን የተሻለች ሀገር ለማስረከብ በጋራ መትጋት እንደሚገባ ማሳሰባቸዉን ኢዜአ ዘግቧል

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review