AMN- ሐምሌ 10/2018 ዓ.ም
በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ሃገራዊ ምክክር ለትውልድ የሚበጅ ውጤት ከማምጣት ባሻገር ዘላቂ ሰላምን ለማጽናት የሚያስችል ነው፡፡
ሃገራዊ ምክክሩ ዘላቂ ሰላምና ብሔራዊ አንድነትን ለመፍጠር የሚያስችል፣ ለረጅም ዘመን የሚጠቅም፣ ልማት የሚያመጣ እንዲሁም ሰላምን የሚያጸና እንደሆነ ይታመናል፡፡
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው የሃገራዊ ምክክር ጉባዔ ከዚህ በፊት የነበሩ ሥህተቶች የሚስተካከሉበት እና የፖለቲካ ስብራትም የሚጠገንበት አጋጣሚ ነው።
የሀገራዊ ምክክሩ አለመግባባቶችን እና ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ለሚደረገው ጥረት እንዲሁም ለዘላቂ ሰላም መረጋገጥ ጉልህ ሚናም ይጫወታል፡፡

በዚህም በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በየጊዜው መልካቸውን እየቀያየሩ የሚስተዋሉት ግጭቶች፣ ልዩነቶች እና አለመግባባቶች መፍተሄ የሚያገኙት ቁጭ ብሎ በመምከር መሆኑን ብዙዎች ያነሳሉ፡፡
ሃገራዊ ምክክሩ የብዙ ዓመታት የዕዳ ክምችትን፣ የትውልድ ቁርሾን፣ የቆዩ ልነቶችንና አለመግባባቶችን ይፈታል፡፡
በአዲስ አበባ እየተካሄደ ያለው የሀገራዊ ምክክር ጉባዔ የትናንትናውን ችግር በመፍታት ለነገ መልካም መሰረት ለማኖርም የሚያግዝ ሲሆን የጋራ የሆነ መፍትሄም የሚያመጣ ነው፡፡

ሃገራዊ ምክክሩ የሚሳካው የእያንዳንዱ ተሳታፊ ጥያቄ ማንንም የማይጎዳ ይልቁንስ ሁሉንም መጥቀም የሚችል ጉዳይ ሲሆን ነው፡፡
ይሄም ሃገራዊ ምክክሩን ፍሬያማ የሚያደርግ እና ለአብሮነት ትልቅ መሰረት የሚጥል ሲሆን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም መከበርም ቁልፍ ሚና ይጫወታል፡፡
ሃገራዊ ምክክሩ አንድነቷ የተጠናከረና ዘላቂ ሰላም የሰፈነባት ኢትዮጵያን ለመገንባት ትልቅ መሰረት የሚጥል ነው፡፡

ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ስታከናውነው የቆየችው የሃገራዊ ምክክር ሂደት አሁን ላይ የመጨረሻና ወሳኝ ምዕራፍ ላይ የደረሰ ሲሆን በሃገራዊ ምክክር ጉባዔው ላይ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ ክፍሎች የተወጣጡ ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ እየመከሩ ነው፡፡
የሻምበል ምህረት