AMN- ሐምሌ 16/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እያከናወነ ያለው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ዛሬም ቀጥሎ ተከናውኗል፡፡

በዛሬው ዕለትም በሙያቸው፣ በትምህርት ዝግጅታቸው እና ለአጀንዳ ሃሳቦቹ ባላቸው ሙያዊ ቅርበት በኮሚሽኑ የተመለመሉት የባለሞያዎች ቡድን፤ በስምንት ዐቢይ ቡድኖች በመከፋፈል በእያንዳንዱ የአጀንዳ ሀሳብ ላይ ገለጻ ሰጥተዋል፡፡

የባለሞያዎቹ ስብስብ የሚያደርጉት ገለጻ ተመካካሪዎች በአጀንዳዎቹ ላይ ሳይንሳዊ ምልከታን እንዲያገኙ የሚያስችል ነው፡፡

ተመካካሪዎች ከሐምሌ 13 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በንዑስ ቡድኖች ተደልድለው ከተወያዩ በኋላ የተሰጠው የባለሙያዎች ገለጻ፤ በቀጣይ ቀናት ለሚደረጉ ምክክሮችና ውሳኔዎች አዎንታዊ እገዛ እንደሚያደርግ የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

በነገው ዕለት ደግሞ ተመካካሪዎቹ ወደ ንዑስ ቡድኖች ተመልሰው በአጀንዳ ሃሳቦቻቸው ላይ የሚያደርጉትን ምክክር ይቀጥላሉ፡፡