AMN መስከረም 8/2019
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ2026 የስካይትራክስ የዓለም አየር መንገድ ሽልማት ለዘጠኝ ተከታታይ ዓመት በአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ በመባል ሽልማትን አግኝቷል።
አየር መንገዱ በአፍሪካ ምርጥ የቢዝነስ ክላስ እና በአፍሪካ ምርጥ የኢኮኖሚ ክላስ አገልግሎት ሽልማቶችንም ተቀብሏል።
የአፍሪካ ቀዳሚው አየር መንገድ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ2026 የSKYTRAX የዓለም አየር መንገድ ሽልማቶች ላይ ለዘጠኝ ተከታታይ ዓመት በመመረጥ የአህጉሪቱ ቁጥር አንድ አየር መንገድነቱን አረጋግጧል።
ከዚህ ታላቅ እውቅና በተጨማሪ አየር መንገዱ በተለያዩ የአገልግሎት ዘርፎችም ሽልማቶችን አግኝቷል። ሽልማቶቹም በአፍሪካ ውስጥ ምርጥ አየር መንገድ፣ በአፍሪካ ውስጥ ምርጥ የኢኮኖሚ ክላስ አገልግሎት አሰጣጥ እና በአፍሪካ ምርጥ የቢዝነስ ክላስ የሚሉት ናቸው፡፡
ሽልማቶቹ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለጥራት ያለውን የማይናወጥ ቁርጠኝነት እንዲሁም በዓለም ዙሪያ ያሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደንበኞች በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ ያላቸውን እምነትና ታማኝነት ያንፀባርቃሉ።
ዕውቅናው አየር መንገዱ የላቀ አገልግሎት ለመስጠት፣ ልዩ የደንበኞችን እርካታ ለመጠበቅ እና በዓለም አቀፍ አውታረ መረቡ ውስጥ እንከን የለሽ የጉዞ ልምድ ለማቅረብ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያጎላ ነው።
በተጨማሪም የአየር መንገዱን ሰራተኞች ያላሰለሰ ጥረት የሚያጎላ ሲሆን፣ በአፍሪካ ግንባር ቀደም የአቪዬሽን ቡድን መሆኑን ያረጋግጣል።
ሽልማቶቹ አየር መንገዱ የአገልግሎቶች እና የአሠራሮች ደረጃ በመጠበቅ ረገድ ያለውን ቁርጠኛነት የሚያረጋግጥ መሆኑን የአየር መንገዱ መረጃ ያመላክታል፡፡