የአትሌት ትዕግስት አሰፋ የሴቶች ብቻ ማራቶን የዓለም ክብረወሰን በዓለም አትሌቲክስ በይፋ ጸደቀ

AMN- ሐምሌ 16/2018 ዓ.ም

የዓለም አትሌቲክስ 2026 የመጀመሪያዎቹ አምስት ወራት ውስጥ የተመዘገቡ የዓለም ክብረወሰኖችን ማጽደቁን ይፋ ባደረገበት መግለጫ የኢትዮጵያዊቷ ጀግና አትሌት ትዕግስት አሰፋ የሴቶች ብቻ ማራቶን የዓለም ክብረወሰን በይፋ መጽደቁን አረጋግጧል።

አትሌት ትዕግስት አሰፋ በ2026 የለንደን ማራቶን ውድድር ላይ ድንቅ ብቃቷን በማሳየት ውድድሩን 2 ሰዓት ከ15 ደቂቃ ከ41 ሰከንድ በሆነ አስደናቂ ሰዓት አጠናቃ መግባቷ ይታወሳል።

አትሌት ትዕግስት አሰፋ ቀደም ሲል በበርሊን ማራቶን ያስመዘገበችውን የዓለም ድንቅ ሰዓት ተከትሎ አሁን ደግሞ በሴቶች ብቻ ማራቶን የተመዘገበውን የዓለም ክብረወሰን በስሟ ማድረጓ ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ታሪክ ሌላ ታላቅ ምዕራፍ ከፍቷል።

ይህ በይፋ የጸደቀው የዓለም ክብረወሰን የአትሌት ትዕግስት አሰፋን ጠንካራ የልምድ እና የትግል መንፈስ የሚያሳይ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያውያን ሴት አትሌቶችን በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ያለውን የበላይነት እንደገና ያረጋገጠ መሆኑን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review