የአዲስ አበባ የክረምት እግር ኳስ ውድድርን ስታዲየም ዙሪያ አሸነፈ

AMN- ነሐሴ 10/2018 ዓ.ም

በሽሮ ሜዳ እና ስታዲየም ዙሪያ ክለቦች መካከል የተካሄደው የአዲስ አበባ የክረምት እግር ኳስ ውድድር የፍጻሜ ጨዋታ በስታዲየም ዙሪያ አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

በጨፌ ሜዳ በተካሄደው የፍጻሜ ግጥሚያ ፣ መደበኛው የጨዋታ ጊዜ ባዶ ለባዶ የተጠናቀቀ ሲሆን ፣ ስታዲየም ዙሪያ በመለያ ምት 5 ለ 4 በሆነ ውጤት የዋንጫ ባለቤት ሆኗል፡፡

ለአንድ ወር ሲካሄድ የቆየው የአዲስ አበባ የክረምት እግር ኳስ ውድድር 24 ክለቦች ተሳትፈውበታል፡፡

ዋንጫውን ያሸነፈው ስታዲየም ዙሪያ የአንድ ሚሊየን ብር ተሸላሚ ይሆናል፡፡

የአዲስ አበባ የክረምት እግር ኳስ ውድድርን የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከቤላ ስፖርት ጋር በመተባበር አዘጋጅተውታል፡፡

በውድድሩ የመዝጊያ ስነ ስርዓት ላይ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን ፕሬዘዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አሰግደው ኃይለጊዮርጊስ ፣ ምክትል የቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ ፣ ኢንትራክተር አብርሃም መብራቱ እና የኢትዮጵያ ቡናው አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ተገኝተው ጨዋታውን ታድመዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review