AMN – ነሐሴ 22/2018 ዓ.ም

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ከታይላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲሃሳክ ፉዋንግኬትክየው ጋር በብሔራዊ ቤተመንግሥት ተወያይተዋል።
የታይላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲሃሳክ ፉዋንግኬትክየው ለይፋዊ የስራ ጉብኝት እና ታሪካዊውን “የታይላንድ-አፍሪካ ኢኒሼቲቭ” በይፋ ለማስጀመር አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል።

ዛሬ ከሰዓት ብኋላ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጋር በብሔራዊ ቤተመንግሥት ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም በኢትዮጵያ እና በታይላንድ መካከል እያደገ የመጣውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ወደ ላቀ ደረጃ ማሻገር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸው ተገልጿል።