አዲስ አበባ የተሽከርካሪ ማቆሚያ ችግር በማቃለል ዕመርታ እያመጣች ነው

AMN – ነሐሴ 22/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ ይስተዋል የነበረውን የተሽከርካሪ ማቆሚያ ችግር ለማቃለል በርካታ ውጤታማ ሥራዎች ተሰርተዋል፡፡

በመዲናዋ ከለውጡ በፊት በአንድ ጊዜ 3ሺ ተሽከርካሪ ብቻ የማቆም አቅም ብቻ የነበረ ሲሆን በጥቂት ዓመታት ወደ 170 ሺህ አድጓል፡፡

በከተማዋ የተሽከርካሪዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ ከተማዋን የተሽከርካሪ ማቆሚያ ችግር ሙሉ ለሙሉ ለመቅረፍ፤ በጎተራ፣ በቦሌ፣ በየካ እና በቀበና እካባቢዎች ዘመናዊ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች በመገንባት የትራፊክ ፍሰትን ማቀላጠፍ ተችሏል፡፡

እነዚህ ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ተርሚናሎች፣ ፕላዛዎች፣ ሱቆች፣ የህፃናት መጫዎችና ማረፊያ ቦታዋችን ያካተቱ እንዲሁም የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ ማድረጊያ ቦታዎች እና ካፍቴሪያ ጨምሮ ንጹህ መፀዳጃ ቤት እና ለተለያዩ አገልግሎት የሚሆኑ ቢሮዎች አሟልተው የያዙ ናቸው፡፡

ይህም የትራፊክ ፍሰቱን ከማቀላጠፍ በተጨማሪ ለሰው ክብር ቅድሚያ የሚሰጡ እና ተገልጋዩን ከዝናብና ከፀሀይ እንግልት እንዳሳረፉ ከአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በትራፊክ መጨናነቅ ይባክን የነበረውን ጊዜና ጉልበት በመታደግም ከተማዋን የምቾት ገፅታ አላብሰዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review