AMN – ነሐሴ 22/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህብረተሰቡን እንግልት ለማስቀረት እና የአገልግሎት አሰጣጡን በቴክኖሎጂ ለማዘመን የጀመረው “አዲስ መሶብ” የአንድ ማዕከል አገልግሎት የከተማዋን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ እያፋጠነው ይገኛል።
ይህ ማዕከል የከተማ አስተዳደሩን እና የፌደራል ተቋማትን አገልግሎቶች በአንድ ጣሪያ ስር በማካተት፣ መሰረታዊ የመንግስት አገልግሎቶች ለተገልጋዮች በቀላሉ እንዲደርሱ አስችሏል።
አሰራሩ ሙሉ በሙሉ በዲጂታል ቴክኖሎጂ የተደገፈ በመሆኑ ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ለመዲናዋ የስሉጥ ከተማ ግንባታ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።

ተገልጋዮች አገልግሎት ለማግኘት የሚያደርጉትን የጊዜ እና የገንዘብ ወጪ የሚቀንሰው ማዕከሉ ፣ የሰዎች ንክኪን በማስቀረት ብልሹ አሠራርንና ሌብነትን ለመከላከል የሚያስችል ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የሚመራ ነው።

በዜጎች ዘንድ በመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ የሚነሱ እንግልቶችን እና ቅሬታዎችን ለመቅረፍም የአዲስ አበባ ከተማን ተሞክሮ በመውሰድ ክልሎችና ሌሎች ከተማ አስተዳደሮችም የራሳቸውን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እየተገበሩ ይገኛሉ፡፡
ለዜጎች በቴክኖሎጂ የታገዘ ፈጣን፣ ተአማኒ፣ ፍትሐዊና ተደራሽ የመንግስት አገልግሎት ለመስጠት ሲባል ሥራ የጀመረው “አዲስ መሶብ” የህዝብን እንግልት በማስቀረት ሙስናን በመከላከል ረገድ አበረታች ውጤቶችን ማስመዝገብ ችሏል።
በበረከት ጌታቸው