ከንቲባ አዳነች አቤቤ “የቅድመ ልጅነት እድገት ሻምፒዮን” ተብለው እውቅና ተሰጣቸው

AMN-ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዓለም አቀፉ Act For Early Years ኢኒሼቲቭ “የቅድመ ልጅነት እድገት ሻምፒዮን” ተብለው እውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡

ይህ እውቅና የከንቲባ አዳነች አቤቤ አመራራቸውንና የከተማ አስተዳደሩ ለሕፃናት እድገት እያደረገ ያለውን ኢንቨስትመንት በተለይም በ”የአዲስ አበባ የወደፊት ተስፋ የቅድመ ልጅነት እድገት ተነሳሽነት” የተሰጠ እውቅና ነው።

ኢኒሼቲቩ ቀዳማይ ልጅነትን በመንግሥታት ፖሊሲዎች እና በዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት አጀንዳ ማዕከል ላይ ለማስቀመጥ በትኩረት ይሰራል።

ይህን እውቅና የተሰጠው ከቀድሞው የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም አቀፍ ትምህርት ልዩ መልዕክተኛ ጎርደን ብራውን በኩል የኢኒሼቲቭ አጋሮች በመወከል ሲሆን፣ UNICEF እና UNESCOን ጨምሮ ከተለያዩ አጋር ተቋማት ጋር በመተባበር የተሰጠ ነው።

እውቅናው አዲስ አበባን በአፍሪካ የቀዳማይ ልጅነት እድገት የከተማ አመራር ተምሳሌት ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያጠናክረው እንደሚታመን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review