የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ለተከታታይ ዓመት የዝውውር ክብረወሰን አሻሻለ

AMN-ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም

የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የክረምት የዝውውር መስኮት ትናንት ለሊት በይፋ ተዘግቷል። የዝውውር መስኮቱ የምንግዜም ከፍተኛ ገንዘብ የወጣበት ሆኗል።

የሊጉ ክለቦች በአጠቃላይ 3.4 ቢሊየን ፓውንድ ወጪ አድርገዋል። በትናንትናው የመዝጊያው ዕለት ብቻ የ475 ሚሊየን ፓውንድ ዝውውር ተከናውኗል።

የዝውውር መስኮቱ ከመጠናቀቁ ጥቂት ጊዜያት በፊት ኢንዞ ፈርናንዴዝን ከቼልሲ ያስፈረመው ማንችስተር ሲቲ 458 ሚሊየን ፓውንድ በማውጣት ከሌሎቹ ልቆ ተገኝቷል።

የይህም ሊቨርፑል ያለፈው ዓመት ይዞት የነበረውን በአንድ የውድድር ዓመት ከፍተኛ ወጪ የማውጣት ክብረወሰንን አሻሽሏል። የመርሲሳይዱ ክለብ ያለፈው ዓመት የዝውውር ወጪው 415 ሚሊየን ፓውንድ ነበር።

ሲቲ በግዢ ብቻ ሳይሆን በሽያጭም ቀዳሚ ሆኖ ተቀምጧል። የኢንዞ ማሬስካ ቡድን ከለቀቃቸው በርካታ ተጫዋቾች 304 ሚሊየን ፓውንድ ወደ ካዝናው አስገብቷል።

ቼልሲ ከማንችስተር ሲቲ በመቀጠል ከፍተኛ ወጪ ያወጣ ክለብ ነው። የምዕራብ ለንደኑ ክለብ 349 ሚሊየን ፓውን ለተጫዋቾች ዝውውር ወጪ አድርጓል። ነገር ግን ቼልሲ ወጪውን በሽያጭ አካክሷል። 382 ሚሊየን ፓውንድ የደረሰው የሽያጭ ገንዘቡ ከግዢው ልቆ ተገኝቷል።

ሌላኛው የለንደን ክለብ ቶተንሃም 302 ሚሊየን ፓውንድ በመክፈል ከወጪ ዝርዝር ውስጥ 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

በአጠቃላይ በሊጉ ከሚሳተፉ 20 ክለቦች 11ዱ የራሳቸውን ክብረወሰን አሻሽለው ተጫዋች አስፈርመዋል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review