ኮርፖሬሽኑ ከ2 ሺህ 500 በላይ የሚሆኑ ሱቆችን ግንባታ በይፋ አስጀመረ

AMN ጳጉሜን 3/2018

የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በዛሬው ዕለት ከ2 ሺህ 500 በላይ የሚሆኑ ሱቆችን ግንባታ በይፋ አስጀምሯል።

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ረሻድ ከማል (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት ተቋሙ በተለያዩ መልኮች ከነበረበት አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ በሪፎርም ወደ ትርፋማ ምዕራፍ መሸጋገሩን ገልጸዋል።

በዚህም ተቋሙ ትርፉን በ42 እጥፍ ማሳደግ መቻሉንና በዛሬው ዕለትም ከ2ሺ 500 በላይ የሚሆኑ ሱቆችን ግንባታ በይፋ ማስጀመሩን ተናግረዋል።

በዛሬው ዕለት የተጀመረው ግንባታ በ4 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ወጪ በአልሚዎች ትብብር የሚገነባ ሲሆን ባለስድስት ወለል ሕንፃና በቂ የመኪና ማቆሚያ፣ ዘመናዊ መዝናኛ ቦታዎችን ከሱቆች ጋር የያዘ ነው።

ዋና ስራ አስፈጻሚው በሱቆቹ ለልማቱ የሚነሱት 230 ነባር ተከራዮችን ጨምሮ ተጨማሪ ዜጎች እድል እንደሚፈጠርላቸውም አስታውቀዋል።

ኮርፖሬሽኑ በአንድ ዓመት ውስጥ አስር ህንፃዎችን ለማጠናቀቅ እቅድ መያዙንና ወደ 10 ሺ ለሚሆኑ ሰዎች የስራ እድል መፍጠር የሚችሉ ግንባታዎች እየተሰሩ እንደሚገኙም አንስተዋል።

በሌላ በኩል የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በመርካቶ ያስገነባውቸን 399 ሱቆችንም በዛሬው ዕለት ማስመረቁን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review